Freitag, 22. Dezember 2006

ከመናፍቃውያን ቡድን መውጣት

ለዚህ Blog ርእስ ምክንያት ሰሞኑን ከአገር ቤት የመጡ ካሴቶች መናፍቃውያን ቡድን ገብተው የወጡ ዜጎች የሰጡት አሳዛኝና አሳፋሪ ምስክርነት ሲሆን እነዚህ ምስኪን ዜጎች ቡድኑን ለቀው ሊወጡ ሲሉ አብዛኛዎቹ ያጋጠማቸው አገር አቀፋዊ የስነልቦና የአካልና የጤና ችግር በጣም አሳዛኝ ሲሆን ይህንን አውዲዮ ካሴት በማሰላሰል በአንድ ወቅት በEthio Cult Information Centre (ECIC) http://www.saveethiopians.net/ ድህረ ገጵ ላይ ባለ ሊንክ ያገኝሁት የአለም አቀፉ ጰረ መናፍቃን ድርጅት ድህረ ገጵ ላይ Association of Former Pentecostals (AFP), http://ex-pentecostals.org/ የተጳፈውን እንደቀይ መብራት አስደንጋጭና አስጠንቃቂ ጵሁፍ ለውይይታችን መነሻ እንዲሆን ልጠቀምበት ወሰንን::
Source : - Association of Former Pentecostals (AFP), http://ex-pentecostals.org/
"Leaving a Pentecostal or non-denominational Charismatic congregation is a difficult journey for many. At Association of Former Pentecostals (AFP), you'll find a network of individuals that have been assisting those who question their involvement with these faiths through an ever-growing resource database (including links, personal essays, news and information), and through our thriving forums (our most popular feature)."

እንግዲህ ይህንን ያክል የማፍያዊ ክፋት ዝናን ያተረፈው የመናፍቃውያን አምላክ ነኝ ባይ በአገራችንም ብዙ ዜጎች መናፍቃውያን ድርጅትን ለቀው ወደ እናት ቤ /ክ ሲመለሱ የሚያስቸግራቸውና የሚያሰቃያቸው ሲሆን ለዚህም በቅርቡ በቪዲዮን ያየነውና የሳሙኤል ምስክርነቶችን ሁላችንም ማስታወሱ በቂ ማስረጃ ነው :: እንግዲህ እነዚህን ሁለት አሳዛኝ ታሪኮች መሰረት በማድረግ ከዚህ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ መነሻ አድርገን እንድንወያይበትና ወደፊት ከመናፍቃውያን ቡድን የሚወጡ ዜጎችን እንዴት አድርገን እንደዚህ አይነት ችግር ውስጥ ሳይገቡ መውጣት እንደሚችሉ ሀሳባችሁን እንድትሰጡ እጋብዛለሁ ::

ጥያቄዎቹ??

  1. ለምን ሰዎች ከመናፍቃውያን ቤ /ክ ሲወጡ ይቸገራሉ ?
  2. ማመን አለማመን በግዴታ ወይስ የሰው ልጅ መብቱ ነው ?
  3. በመናፍቃውያኑ በኩል ያለው መንፈስ እውነት እየሱስ ከሆነ እንዴት በጰበል ሰይጣን ነኝ ያላል ?
  4. እንዴት እንደዚህ አይነት ችግር ውስጥ የገቡ ሰዎችንና ከመናፍቃውያን ሊወጡ የሚፈልጉ ወገኖችን መርዳት ይቻላል ?


ለውይይታችን መነሻ እነዚህ እነኚህን የብዙ ዜጎችን አላምንም በማለታቸው ብቻ የሚገኙበትን ስቃይ የሚያሳዩ ሊንኮች ሲሆኑ እናንተም በአካባቢያችሁ የምታውቁትን በየድህረገጱና በአውዲዮ መልክ የወጡና ያልወጡ የምናውቃቸው ዜጎች የስቃይ ህይወት ብትጨምሩበት የችግሩን አገር አቀፋዊ ስፋት ለማየት የሚያስችል ሲሆን የውይይታችን አላማ አላምንም ብለው ወደ እናት ቤ /ክ በመመላሳቸውም ይሁን በሌላ መንገድ በማመናቸውና የመናፍቃኑንን እየሱስ አላምንም በማለታቸው መብታቸው ክብራቸው በመናፍቃውያኑ በኩል እየሱስ ነኝ በሚለው መንፈስ የሚነኩ ወገኖችን ለማዳንና ለሌሎች ለማይውቁም ለትምህርት ስለሆነ ለሁላችንም አስተማሪና ገንቢ የሆነ ሀሳባችሁን አክሉበት::

ውድ የብሎጉ አንባቢያን:- የመንደሩ ወይም በአለም አቀፍ ደረጃ (International Standard) ተቀባይነት በሌለው መልኩ በአገር አቀፉ ደረጃ በቪዲዮው እንደሚያዩት በጴንጤ በኩል እየሱስ ነኝ ብሎ የመጣው በጰበል ከቱርክ የመጣሁ አጋንንት ነኝ ቅብጥርሴ እንያለ ዜጎችን ሲያሰቃይና ሲያስቸግር ያላፈረ እውነቱን በግልጵ በብሎጉ አማካኝነት በቪዲዎቹ የተደገፈ መረጃውን ማውጣትና ወንጀሉን በማጋለጥ በአምልኮ ስም ተጠቂ ዜጎችን መብታቸውን ስለሚያስከብርና ሌሎችን ወደፊት ሳያውቁ መታለልና ጥቃት ስለሚጠብቅ ሚስጥር (Taboo) ማድረጉ አላስፈለገም::

Keine Kommentare: